ስለኛ

ድምፂ ወያነ ትግራይ (ድወት) የደርግን ስርዓት ለመጣል በህወሓት መሪነት የተካሄደውን የትጥቅ ትግል ለማጠናከር መስከረም 30 ቀን 1972 በነጻ የኤርትራ ምድር ስርጭቱን የጀመረ፤ ሐምሌ 8 ቀን 1978 በትግራይ ነፃ መሬት ወልቃይት ልዩ ቦታ ማይ ሙሴ ላይ የራሱን ሬዲዮ ጣቢያ በመትከል ስርጭቱን ቀጠለ።  ከደርግ መንግስት ውድቀት በኋላ አገራዊና ክልላዊ ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ለህዝቡ በማቅረብ ልማትና ዴሞክራሲን በማስፈን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት እየሰራ የመጣ፤ ከየካቲት 1997 ጀምሮ እንደ ብሮድካስት ሚዲያ ኩባንያ በክልል እና በፌደራል እውቅና ተመዝግቦ በአጭርና መካከለኛ የሬድዮ ሞገድ ስርጭቱን እያስተላለፈ ተደማጭነትን ያገኘ ሚድያ ሆኖ ቀጠለ። በ2001 ዓ.ም ከአጭርና መካከለኛ መጎድ ብሄራዊ ሬድዮ ተጨማሪ የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ከፍቶ፣ በሂደት ወደ 7 ኤፍ ኤም ጣቢያዎች በማስፋፋት ተደራሽነቱን እያሰፋ የመጣ ድወት በ 2010 ዓ.ም ደግሞ የትግራይን እሴት እና ባህል ያተኮሩ ዜናዎች ፣ ትምህርታዊ እና መዝናኛ ፕሮግራሞች በቲቪ መስኮት ይዞ በመምጣት ታላቕ ተወዳጅነት ያገኘ ሲሆን፤ ከአውዳሚው ጦርነት በኋላም ከዚህም ከዚያም ያገኛቸው መሳሪያዎች ተጠቅሞ ለስርጭት የበቃ ሲሆን ሁሌም ተመራጭ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ሚዲያ ሆኖ ለመቀጠል የሚተጋ ተራማጅ የግል ሚዲያ ነው።

 

Free Location SVG, PNG Icon, Symbol. Download Image.    መቐለ፣ ትግራይ

Telephone Vector Icons free download in SVG, PNG Format   +251344410546

Fax Icon - Blue Fax Machine Icon - CleanPNG / KissPNG    +25134405485

Postal Address Icon PNG, Vector, PSD, and Clipart With Transparent  Background for Free Download | Pngtree   450

Understanding the Importance of Email Icons - blog - imaginethatcreative.net   dwinfo@dimtsiweyanetigrai.com